Asset Publisher

የሳይበር ደህንነት

የሳይበር ደህንነት መረጃን፣ የመረጃ መሰረተ ልማትንና ሌሎች ከሳይበር ጋር የሚተሳሰሩ መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም ስዎችን አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚፈጥሩ ሳይበር ጥቃቶች መጠበቅን ያለመ ሲሆን በዋናነትም የመረጃ እና መሰረተ ልማትን ምስጢራዊነት፣ ተአማኒነትን እና ተደራሽነትን ማረጋገጥ ላይ የሚያተኩር ነው። ሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚቀመጡ መፍትሄዎች ሁሉን አቀፍ መሆን ያለባቸው ሲሆን እነዚህም መፍትሄዎች በዋናነት አስፈላጊውን የደህንነት ቴክኖሎጂ መተግበርን፣ ደህንነት ሊያሳልጥ የሚችል ስርዓት እና አደረጃጀት መዘርጋትን እና የሰዎችን ንቃተ-ህሊና ማሳደግን ያካትታል።