በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ የለማዉ “ቪዚት ኢትዮጵያ” ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ

Geneste Applicaties

Contentverzamelaar

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ የለማዉ “ቪዚት ኢትዮጵያ” ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ የለማዉ “ቪዚት ኢትዮጵያ” ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ wo, 9 jul 2025

የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሜጀር ጀነራል ዶ/ር አሕመድ ናስር አል ራኢሲ በኢመደአ የስራ ጉብኝት አካሄዱ

የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሜጀር ጀነራል ዶ/ር አሕመድ ናስር አል ራኢሲ በኢመደአ የስራ ጉብኝት አካሄዱ ma, 7 jul 2025

የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ተፈረመ

የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሦስትዮሽ የስምምነት ሰነድ ተፈረመ wo, 2 jul 2025

የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ተቀባይነት በማግኘት እውቅና ተሰጠው

የኢትዮጵያ የሩት ሰርተፊኬት ባለስልጣን በዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ተቀባይነት በማግኘት እውቅና ተሰጠው wo, 25 jun 2025

Contentverzamelaar

null በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ የለማዉ “ቪዚት ኢትዮጵያ” ፕላትፎርም በይፋ ተመረቀ

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ቪዚት ኢትዮጵያ (Visit Ethiopia) መተግበሪያ ፕሮጀክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን በከፍተኛ ትኩረት መሰራቱን ጠቁመዋል።

እንደ ሀገር በቱሪዝም ሴክተር የዲጂታል ግብይትን የሚደግፍ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች የሚሰጥ፣ ንክኪ አልባ ክፍያዎች የተገበረ፣ ቨርቿል ጋይድላይኖች እና ዘመናዊ መሠረተ ልማት መፍጠር ካልተቻለ ተጠባቂዉን ጥቅም ማግኘት እንደማይቻል ገልጸዋል።

በመሆኑም የቱሪዝም ኢንዱስትሪያችንን የበለጠ የማይበገር፣ አካታች እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ዲጂታላይዝ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

ቪዚት ኢትዮጵያ (Visit Ethiopia) መተግበሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተጠቃሚን ያማከለ መተግበሪያ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በተለይም ሀገራዊ የቱሪስት መስህቦቻችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል::

ከዚህ ባለፈ በፕላትፎርሙ የሚከናወኑ ማናቸውም መስተጋብሮች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ታማኒነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆኑ ተደርጎ መሰራቱን ወ/ሮ ትዕግስት ጠቁመዋል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸዉ ቱሪዝም ከቴክኖሎጂ ለውጦች ጋር በእጅጉ የተሳሰረ መሆኑን አንስተዉ በዓለም አቀፍ ገበያ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቱሪዝም ልማት ከዘመን ጋር መዘመንን፣ ከጊዜ ጋር መገስገስን የሚጠይቅ ነዉ ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ሁሉንም ዓይነት የቱሪዝም ልማት እንቅስቃሴዎች በቴክኖሎጂ ማጠናከር እና ከቱሪዝም ገበያ ወቅታዊ ለውጦችና ፍላጎቶች ጋር ማጣጣም ትኩረት የሚሻ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ይህ ዛሬ በይፋ የተመረቀዉ Visit Ethiopia የተሰኘ ዲጅታል ፕላትፎርም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እና የቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን ኢትዮጵያ ምቹና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ መሆኗን ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-