ኢመደአ እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

入れ子になったアプリケーション

アセットパブリッシャー

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ሀገሪቱ የፈጠረችዉን የቴክኖሎጂ አቅም ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሆነ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ሀገሪቱ የፈጠረችዉን የቴክኖሎጂ አቅም ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሆነ ተገለጸ 月, 12 5 2025

በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለበትን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለበትን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት ተገለጸ። 月, 12 5 2025

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ 水, 7 5 2025

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ 金, 25 4 2025

アセットパブリッシャー

null ኢመደአ እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የአዳማ ከተማ አስተዳደር "የስማርት አዳማ" ፕሮጀክት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ እና የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተፈራርመዋል፡፡

“የስማርት አዳማ” ፕሮጀክት የእስካሁኑ የስራ አፈጻጸም በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ ውጤት ለሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም ተምሳሌት እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ መሆኑን የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር “የስማርት አዳማ” ፕሮጀክት እውን እንዲሆንና ከተማዋን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሂደት አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍና የማማከር ሥራ እንደሚሰራ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ኢመደአ በራስ አቅም ያለማቸውን የሳይበር ደህንነት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለከተማ አስተዳደሩ በማስታጠቅ፣ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን የመስጠት፣ የሳይበር ደህንነት ፍተሻና ግምገማ አገልግሎት እና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን እንደሚሰራ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናግረዋል፡፡

በ “ስማርት አዳማ” የስራ ሂደት ግምገማ ላይ የአደማ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኦሮሚያ ከተሞች ክላስተር አስተባባሪ መስፍን መላኩ፣ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ዴኤታ ፋንታ ደጀንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።