አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Beágyazott alkalmazások

Tartalom megjelenítő

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ሀገሪቱ የፈጠረችዉን የቴክኖሎጂ አቅም ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሆነ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ሀገሪቱ የፈጠረችዉን የቴክኖሎጂ አቅም ለዓለም የምታሳይበት መድረክ እንደሆነ ተገለጸ H, 12 máj. 2025

በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለበትን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለበትን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት ተገለጸ። H, 12 máj. 2025

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ Sze, 7 máj. 2025

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ P, 25 ápr. 2025

Tartalom megjelenítő

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡