“ቤተሰብ የሀገር መሠረት” - የኢመደአ የቤተሰብ ቀን በድምቀት ተከበር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመታዊ የቤተሰብ ቀን የአስተዳደሩ ሰራተኞችና ልጆች በተገኙበት “ቤተሰብ የሀገር መሠረት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት ተከበረ፡፡

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በበአሉ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አስተዳደሩ ተልዕኮውን በብቃት ለማሳካት አባላት እና የአባላት ቤተሰቦች ያላቸው ሚና ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ቀኑ በተቋም ደረጃ ሲከበር የቤተሰብ ጉዳይ በአስተዳደሩ ዘንድ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑንና ጤናማ፣ ጠንካራ እና መልካም ቤተሰብ ጤናማ የስራ ከባቢን ለመፍጠርና የአስተዳደሩን ተልእኮ ለማሳካት የሚኖረውን ሚና በሚያሳይ መልኩ በጋራ፣ በፍቅርና በሕብረት ለማክበር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገርን ኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ደህንነት የመጠበቅና የሳይበር ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ትልቅ ሀገራዊ ተልኮ የተሰጠው ተቋም ነው፡፡

በተለይም የአስተዳደሩ የሥራ ባሕሪ 24 ሰአት 7ቱንም ቀን (በአላትን ጨምሮ) በሥራ ቦታ ላይ መገኘትን የሚጠይቅ ከመሆኑ አኳያ የተቋማችን አመራርና ሰራተኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማሳለፍ የሚገባቸውን ጊዜ በአግባቡ ላያሳልፉ ይችላሉ፤ ከዚህ አኳያ ይህንን በመረዳት ቤተሰቦች ለምታደርጉት ድጋፍ ኢመደአ ያለውን ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ያቀርባል ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ብቁ ተቋምና ታላቅ ሀገር ለመገንባት ቤተሰብ ላይ መስራት ፋይዳው የጎላ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከዚህ አኳያ ለተቋማችን ተልዕኮ ስኬት የእያንዳንዱ ሰራተኛ ቤተሰብ ያለውን ሚናና ድርሻ በአግባቡ በመረዳት ኢመደአ ለተቋሙ ሰራተኞችና ለቤተሰቦቻቸው ተገቢውን ትኩረት ይሰጣል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመታዊ የቤተሰብ ቀን ዘንድሮ ሰኔ 7/2017 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረ ሲሆን፤ በአሉ በቀጣይ በየአመቱ እንደሚከበር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡