ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

التطبيقات المتداخلة

ناشر الأصول

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ الجمعة, ٢٥ Apr ٢٠٢٥

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ

40 የሚሆኑ የሳይበር ታለንት ማዕከል ወጣት ሴቶች በዓለም አቀፉ “የወጣት ሴቶች የአይሲቲ ቀን” ላይ ተሳተፉ الجمعة, ٢٥ Apr ٢٠٢٥

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ الاثنين, ١٤ Apr ٢٠٢٥

በናይጄሪያ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ኢፕ ዩንዲያንዬ የተመራ ልዑክ በኢመደአ የስራ ጉብኝት አደረገ

በናይጄሪያ የመከላከያ ሰራዊት የመረጃ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ኢፕ ዩንዲያንዬ የተመራ ልዑክ በኢመደአ የስራ ጉብኝት አደረገ الأربعاء, ٩ Apr ٢٠٢٥

ناشر الأصول

null ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ ምህዳር ለመፍጠር ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነትን ማጠናከር እንደሚገባ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገለጹ።

ይህን ያሉት ኢትዮጵያ በብራዚል መዲና ብራዚሊያ በተካሄደው የብሪክስ የሳይበር ደህንነት እና ጥበቃ ስብሰባ ላይ በተሳተፈችበት መድረክ ላይ ነዉ።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ምህዳር ለመፍጠር ሀገር አቀፍ ትብብር እና ዓለም አቀፍ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ በስብሰባው ላይ ስለ ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ገለጻ አድርገዋል።

ፖሊሲው የመንግስት፣ ህዝብ እና የበርካታ ባለድርሻ አካላት የጋራ ተሳትፎን ማዕከል ያደረገ፣ ለቁልፍ የመረጃ መሰረተ ልማቶች እና ለግል መረጃ ጥበቃ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም ለዲጂታል የኢኮኖሚ ተግባራት ደህንነቱ የጠበቀ አሰራርን መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት ዓለም አቀፍ ትብብር እና አጋርነት እንዲጠናከር ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

በብሪክስ ማዕቀፍ አማካኝነት በኢንፎርሜሽን ደህንነት ዘርፍ እድሎችን መጠቀም እና ስጋቶች በጋራ መከላከል እንደሚገባም ነው አምባሳደሩ ያሳሰቡት።

ስብሰባው የብሪክስ አባል ሀገራት የአይሲቲ ደህንነት ይዞ የመጣቸው እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ሀሳቦችን እንዲለዋወጡ እና ሀገራዊ ተሞክሯቸውን እንዲያቀርቡ ምቹ አጋጣሚን መፍጠሩ ተመላክቷል።

አባል ሀገራቱ በጉዳዩ ላይ ብሪክስ ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተመላክቷል።