Skip to Content
  • Drop an Email contact@insa.gov.et
  • Get in Touch +251-113-71-71-14
Back

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አመራሮች በተቋማዊ ለውጥ ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2010- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) አመራር አባላት በኤጀንሲው ልዩ ልዩ የአሰራር ስርዓቶች ዙሪያ የሚያደርጉት ውይይት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በስብሰባው ላይ ተገኝተው የውይይት መድረኩን የከፈቱት የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደተናገሩት ውይይቱ  በዋናነት ተቋሙ ይዞ የተነሳውን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በሁሉም የስራ ዘርፎች የጋራ አቅጣጫ ይዞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለው እንደተናገሩት መንግስት የመደበውን በጀት በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት ለመጠቀምና ለመምራት እንዲሁም የፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓታችንን ለማሻሻል እንዲያስችል የአሰራር መመሪያዎችን አስመለክቶ የጠራ ግንዛቤ መያዝና በመመሪያው መሰረት መፈጸም እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

አቶ ተመስገን አያይዘውም ስልጠናው ተቋሙ ከዚህ ቀደም የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን ለይቶ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር ለመስጠት ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የማያሰሩ የአሠራር ሥርዓቶችም ካሉ ሃሳብ በመስጠት ለመሻሻል የሚያስችል ግብዓት መስጠት ከተሰብሳቢው እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡

ለአራት ተከታታይ ግማሽ ቀናት በሚቆየው በዚህ ውይይት በኢጀንሲው የአሠራር ስርዓትና ህጎች፣ በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር፣ በዕቅድ ዝግጅት፣ በሪፖርት አቀራረብና በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግና ውይይቱም በጉዳዩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ እንደሚያስችል ተገልል፡፡

በዛሬው መድረክ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ጥልቅ ውይይት ተደረገ ሲሆን ውይይቱ በየደረጃው ካሉ የአመራር አባላት ጋር የሚደረግ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡


  የቴክኖሎጂ ዜና

ደህንነቱ የተጠበቀ ሳይበር ለሰላም ፣ ለልማትና ዲሞክራሲ

   ሳይበርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም

ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

ራዕይ

  • በ2017 ዓ/ም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለው እና በሀገሪቱ ህዳሴ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ብሄራዊ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ተቋም እውን ማድረግ፡፡   

ተልዕኮ

  • የአገሪቱን ኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማትን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ፡፡

እሴቶች

  • ተዓማኒነት
  • ሁሌም መማርና ማደግ
  • ልዩነት መፍጠር 
  • ተጠያቂነት

Web Content Display Web Content Display

 
 
INSA

ያግኙን ያግኙን

ስልክ: +251-11-371-71-14
ፖ.ሣ.ቁ: 124498
ኢሜል: contact@insa.gov.et
ፋክስ: +251-11-320 40 37
አድራሻ: አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ