ቲዊተር ከ70 ሚሊየን በላይ አካውንቶችን ማገዱን ገለጸ

ሐምሌ 2/2010፡- የማህበራዊ ሚዲያ ኔትዎርኩ ቲዊተር (Twitter) በየቀኑ የሃሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ያገኛቸውን ከአንድ ሚሊዮን በላይ አካውንቶችን አገልግሎት የማገድ ተግባር ማከናወኑን ገለጸ፡፡

 
ከ336 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ጎብኝዎች ያሉት ቲዊተር በግንቦት እና ሰኔ ወራት ብቻ የተቋሙን የአጠቃቀም መመሪያ በሚጣረስ መልኩ የሃሰት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ያገኛቸውን ከ70 ሚሊዮን በላይ የቲዊተር አካውንቶች መዝጋቱን ይፋ አድርጓል፡፡ 
በዚህም ተቋሙ በተያዘው ሃምሌ ወር ውስጥ በፕላትፎርሙ የሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎችን መጠን መቀነሱን አሳውቋል፡፡


336 ሚሊዮን ብቻ ተጠቃሚዎች ያሉት ቲዊተር ይህን ያክል መጠን አካውንቶችን መዝጋት እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን እሙን ቢሆንም ቲዊተር እና ፌስቡክ የመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች በአሜሪካ እና በዓለም አቀፍ ህግ አውጪዎች በሃሰት መረጃዎች ስርጭት ጋር በተያዘ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡

www.reuters.com