በቲዊተር የሃሰት መረጃዎች 70 በመቶ ከትክክለኛ መረጃዎች የመስፋፋት አቅም እንዳላቸው ተጠቆመ

 

የማሳቹሴትሰ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ባወጡት የጥናት ውጤት በማህበራዊ ሚዲያ ኔትዎርኩ ቲዊተር ከሚለጠፉ መረጃዎች መካከል ሃሰት መረጃዎች ከእውነተኛ ዜናዎች ይልቅ የመስፋፋት አቅማቸው በ70 በመቶ የላቀ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ ችግርም ያለሰዎች ድጋፍ ከሚፈጸሙ የሮቦቶች ተግባቦት የተፈጠረ ችግር አለመሆኑን የገለጸው የጥናቱ ውጤት በሰዎች አማካኝነት የተፈጠረ ነው ብሏል፡፡

ተቋሙ በ3 ሚሊዮን የቲዊተር ተጠቃሚዎች ለተከታዮቻቸው ከተካፈሉ (shared) መረጃዎች መካከል በ126,000 ጽሁፎች ላይ ከ2006 እስከ 2017 ባደረገው ጥናት መሰረት የሃሰት መረጃዎች ከሃቀኛ መረጃዎች በ70 በመቶ የላቀ ሪቲዊት (retweeted) ተደርገዋል ብሏል፡፡

ሁሉም አይነት የሃሰት መረጃዎች ከእውነተኛ መረጃዎች በከፍተኛ መጠን እና ፍጥነት የመስፋፋት አቅማቸው ከፍ ያለ ሲሆን ሃሰተኛ የፖለቲካ መረጃዎች ደግሞ ከሽብር፣ ከተፈጥሮ አደጋዎች፣ ከፋይናንስ ኢንፎርሜሽኖች፣ የተሻለ እንደሚራገብ ጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-usa-cyber-twitter/false-news-70-percent-more-likely-to-spread-on-twitter-study-idUSKCN1GK2QQ