ማሕበራዊ ሚዲያ ለ650ሺ ማይናማራውያን መፈናቀልና ዕልቂት ምክንያት እንደሆነ ተገለጸ

ባሳለፍነው ነሐሴ በማይናማር ለተፈጠረው የመፈናቀልና የጅምላ ግድያ ማህበራዊ ሚዲያ የችግሩ አቀጣጣይ እንደነበር የመንግስታቱ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

በመንግስታቱ ድረሰጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለሙያዎች በምርመራቸው እንዳረጋገጡት በማይናማር ከባድ የመፈናቀል አደጋ መድረሱንና ለዚህ ድርጊት ደግሞ በፌስቡክ የሚለቀቁ የጥላቻ ወሬዎች ከፍተኛውን ድርሻ ማበርከታቸውን ድርጅቱ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡ እንደ ድርጅቱ ገለጻ ከሆነ በማሕበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መልዕክቶች ከልክ ያለፍ ብሔርተኝነትን የሚያጧጡፉና በሃይማኖት ምክንያት ልዩነትን በማስፋት አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ መንገድ እየከፈቱ ነው ብሏል፡፡ ለዚህም በፈረንጆቹ 2017 ዓ.ም በማይናማር 650ሺ የሚሆኑ የሮሂጊያ ሙስሊሞች በዕምነታቸው ምክንያት በተሰነዘረባቸው ጥቃት የመፈናቀልና የዕልቂት አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን በችግሩ የማይናማር የጸጥታ ኃይሎች ሳይቀሩ መሳተፋቸውን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡  በተመድ የዚህ ጉዳይ አጣሪ የሆኑት ያንጊ  ሊ እንዳሳሰቡት ፌስቡክ በሰዎች ህይወት ላይ የደቀነው አደጋ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የየአገራቱ መንግስታት ሁኔታውን በአንክሮ ሊመለከቱት ይገባል ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ሚስተር ያንጊ ሊ አክለው እንዳሉት ፌስቡክ የሰውን ልጅ እርስ በርሱ እንዲጨካከን መንገድ እየከፈተ የመጣ ነው ማለት እችላለሁ ሲሉም የጉዳዩን አሳሳቢነት አንስተዋል፡፡

የፌስቡክ ኩባንያ በበኩሉ ችግሩን መቅረፍ ባይችልም በሠዓቱ የጥላቻ ንግግሮችን ማስወገዱንና የችግሩ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችን ከገጹ ማጥፋቱን ዘገባው አካቷል፡

https://www.reuters.com/article/us-myanmar-rohingya-facebook/u-n-investigators-cite-facebook-role-in-myanmar-crisis-idUSKCN1GO2PN