በፌስ ፌስቡክ የሚለጠፉ ይዘቶችን የሚከታተሉ ተጨማሪ 500 ተቋራጮችን በጀርመን ማሰማራቱን ፌስቡክ ገለጸ

የማህበራዊ ሚዲያው ፌስቡክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሙ ላይ እየተፈጠሩ ያሉ የሃሰት እና የጥላቻ መረጃዎች እየተስፋፉ በመሆናቸው በተቋሙ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል፡፡ ይህን ተከትሎም በገጹ የሚለጠፉ መረጃዎችን ለመከታተል ድጋፍ የሚደርጉ 500 ተጨማሪ ኮንትራክተሮችን በጀርመን ማሰማራቱን አሳውቋል፡፡ ተቋሙ ይህን እርምጃ የወሰደው የጀርመን ህግ አውጪዎች ባለፈው ሃምሌ ወር የማህበራዊ ሚዲያ ተቋማት በገጾቻቸው የሚለጠፉ የጥላቻ አዘል፣ ዘረኛ እንዲሁም የሃሰት መረጃዎችን ከገጻቸው በሳምንት ውስጥ ካላጠፉ እስከ 59 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቅጣት መጣሉን ተከትሎ ነው፡፡

https://www.apnews.com/e1ac98f540b44137a612d6c309744bd4/Facebook-opens-2nd-office-combating-hate-speech-in-Germany