በ21ኛው የዓለም እግርስ ኳስ ዋንጫ 25 ሚሊዮን የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸው ተነገረ

ሰሞኑን በተጠናቀቀው የ21ኛው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ 25 ሚሊዮን የሳበር ጥቃቶችና ተያያዥ ወንጀሎች ማክሸፉን የሩሲያ መንግስት አስታወቀ፡፡ ወንጀሎቹ ያነጣጠሩት በኢንፎርሜሽንና በኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ላይ እንደነበር ያወሳው የሮይተርሰ ዘገባ የተሰነዘረው ወንጀል ምንም ኪሳራ ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል፡፡

በተጠናከረ የወንጀል መከላከል ስራም የዘንድሮው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን በዘገባው ተነስቷል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-soccer-worldcup-russia-cyber/russia-says-it-prevented-25-million-cyber-attacks-other-acts-during-world-cup-idUSKBN1K60DD