ዩሮፖል የተሳሳቱ ምርቶችን ሲሸጡ የነበሩ ከ20,000 በላይ ድረ-ገጾችን መያዙን ገለጸ

ምርቶቻቸውን በቀጥታ (online) ድረ-ገጾች አማካኝነት በሚሸጡ የመገበያያ ማእከሎች ላይ የአውሮፓ ፖሊስ ሃይል (Europol) በከፈተው ድንገተኛ ዘመቻ 20,500 የሚሆኑ ድረ-ገጾች የተሳሳቱ ምርቶችን ሲሸጡ መያዙን ገልጿል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ድረ-ገጾች እጅግ በተራቀቀ መልኩ ምርቶችን የሚሸጡ በመሆናቸው ማጭበርበሪያዎች መሆናቸውን ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ መሆናቸውን ተቋሙ ገልጿል፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች የሞባይል አፕሊኬሽን ስቶሮችን (mobile app stores) እንደ አንድ የመሸጫ ሱቅ አድርገው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡ በድረ-ገጾች ከሚሸጡ የተሳሳቱ ምርቶች መካከልም በሃሰተኛ ዲዛይነር የተሰሩ ሰዓቶች፣ ተአማኒነት የጎደላቸው የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ መድሃኒቶች፣ የህጻናት መጫወቻዎች እንዲሁም የመኪና መቀያየሪያ ክፍሎች እንደሚገኙበት የዩሮፖል መረጃ ገልጿል፡፡

http://www.ibtimes.co.uk/europol-operation-seizes-20000-rogue-websites-peddling-counterfeit-luxury-goods-drugs-1649222