የ12ኛ ዙር 20/80 ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅዳሜ ሰኔ 2 ቀን 2010 ዓ.ም በ2ዐ/80 የቤት መርሀ ግብር የተገነቡ 2ሺ 6ዐ4 ቤቶችን ለእድለኞች በእጣ አስተላልፏል፡፡ እጣ የወጣባቸውን ቤቶች ጨምሮ ለእድለኞች የተላለፉ ቤቶች ወደ 178ሺ ከፍ ብሏል፡፡

በዕለቱ በተካሄደው 12ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ባለ እድል የሆኑ የከተማ ነዋሪዎች በ1 ወር ጊዜ ውጥ የቁልፍ ርክክብ የሚደረግላቸው ሲሆን የቤት ዋጋውም በ11ኛው ዙር ለባለ እድለኞች በተላለፈበት ዋጋ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በመገንባት ላይ ያለውን ከ94 ሺ በላይ ቤቶች በሚቀጥለው ዓመት አጠናቅቆ ለቤት ባለ ዕድለኞች ለማስተላለፍ እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

አጠቃላይ የ12ኛ ዙር (2ሺ 6ዐ4 ቤቶችን) የቤት ዕድለኞችን ዝርዝር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የ12ኛ ዙር 20/80  ቤት ፕሮግራም አሸናፊዎች ዝርዝር