የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 10ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንንና የኢመደኤን ሳምንት በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ምስረታ ምክንያት በማድረግ በየአመቱ ኅዳር ወር መጨረሻ የሚከበረው የኢመደኤ ሳምንትን ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ እንዲሁም 10ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በተመለከተም ኤጀንሲው በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አክብሯል፡፡  

የዘንድሮው የኢመደኤ ሳምንት ታስቦ የዋለው "ምቹ የስራ ከባቢ ለላቀ ስኬትና ውጤታማነት" በሚል መሪ ቃል ሲሆን ኤጀንሲው ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እያደረገ ስላለው ጥረት ግንዛቤ በመፍጠርና ከተቋሙ ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማድረግ ነበር፡፡  

በተመሳሳይም 10ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተሳትፎ ለላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን" በሚል መሪ ቃል ኅዳር 28 ቀን 2008 ዓ.ም በተቋሙ ተከብሯል፡