የሳይበር ወንጀለኞች ዓለምን በየዓመቱ 1.5 ትሪሊዮን ዶለር ያሳጧታል ተባለ

በአሜሪካን አገር በሚገኘው ብሮሚየም የደሕንነት ኩባንያ ስፖንሰርነት በተጠና ጥናት መሰረት የሳይበር ወንጀለኞች አዲስ በዘረጉት መስመር (New criminal platforms) በወንጀሉ የሚያገኙት ዓመታዊ ትርፍ 1.5 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሏል፡፡  ዘጋርዲያን እንደዘገበው ጥናቱ የተካሔደው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም የሳይበር ወንጀለኞች በመጥፎ ድርጊታቸው የንብረት ባለቤት መሆናቸውን እና ዓለምን ደግሞ ለኪሳራ ሊዳርጋት እንደሚችል ያመላከተ ነው ተብሏል፡፡ ወንጀለኞች የሚያካብቱት ትርፍ 860 ቢሊዮን ዶላር ከኦንላይን ገቢያ የሚጭበረበር፣ 500 ቢሊዮን ዶላር ከንግድና ከምርምር ስራ የሚሰረቅ፣ 160 ቢሊዮን ዶላር ከመረጃ ዝውውር እና 1 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ በራንሰምዌር አማካኝነት የሚገኝ ነው ሲልም መረጃው አክሎ ጠቁሟል፡፡

አዲሱ የሳይበር ወንጀለኞች ፕላትፎርም ድንበር የለሽና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ አደገኛ ዕጽ ዝውውር እና አሸባሪነትን ጨምሮ በሁሉም መስክ መሳተፍ የሚያስችል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡  

https://guardian.ng/business-services/cybercrime-profits-estimated-at-1-5-trillion/