ማይክሮሶፍት የዊንዶው 10 የጥቅምት ወር ማሻሻያ ማስቆሙን ገለጸ

 

 

አዲስ አበባ መስከረም 29/2011፡- ማይክሮሶፍት የጥቀምት ወር የዊንዶው 10 ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማሻሻያ አስቁሟል፡፡

ኩባንው ማሻሻያውን ያስቆመው ከተለያዩ ደንበኞች ፋይሎቻቸው እንደጠፉባቸው ሪፖርት በማድረጋቸውን ተከትሎ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡

ማሻሻያውን በተቀመጠው መመሪያ መሰረት ዳውንሎድ ያደረጉ ደንበኞቹም ማሻሻያውን እንዳይጭኑት (install)   ማይክሮሶፍት አሳስቧል፡፡

በደንበኞቹ ጥቆማ መሰረት ችግሩን መመርመሩን እንደሚቀጥል እና እስከዚያው ማሻሻያውን ለጊዜው መግታቱን ኩባንያው በመግለጫው አስፍሯል፡፡

 

https://www.bbc.com/news/technology-45784482