የስውር የኢንተርኔት አገልግሎቶች የህግ ማእቀፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተጠቆመ

 

አዲስ አበባ መስከረም፤ 25/2011፡- ለተለያዩ ተግባራት የሚውሉና በስውር የኢንተርኔት ድሮች በሚደረጉ የመረጃ ማሰባሰብ ላይ ሁሉን አቀፍ የሆነ የመመሪያ ማእቀፎች እንዲዘጋጅ ጥሪ ቀረበ፡፡

ሊዘጋጁ የሚገባቸው ስታንደርዶችም በስውር የኢንተርኔት ድር የሚከናወኑ ምርትና የአገልግሎት ሽያጮችን መገምገም እና ለመግለጽ በአጋዥነት የሚውል መሆን እንደሚገባውም ተጠቁሟል፡፡

የጋራ አቋም እና የህግ ማእቀፎችን ለማስቀመጥ ጥሪ የቀረበውም ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው አብዛኛዎቹ ጥናቶች ወጥነት የሌላቸው እና አሳሳች ሆነው በመገኘታቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ተርቢየም ላብ (Terbium Labs) ከ2013 ጀምሮ ከተለያዩ 18 ምንጮች አደረኩት ባለው ፍተሻ የደህንነት ምርት አቅራቢዎች እና ተመራማሪዎች ከስውር የኢንተርኔት ድር ጋር የዋጋ እና የተሰረቁ አካውንቶች እንዲሁም በማንነት መረጃዎች በ22 ሪፖርቶች ትንተና ማድረጉን ጠቁሟል፡፡

በዚህም የሚወጡ ሪፖርቶች የዴታ ማሰባሰብ ሂደት ላይ እና የናሙና ዘዴዎቻቸው ተከታታይነት የጎደላቸው መሆኑን ተርቢየም ጠቁሟል፡፡

በሳይበር ደህንነት ዙሪያ እየተፈጠሩ ያሉ ፍራቻዎችን ፣ አለመረጋጋቶችን እና እየሰረጹ ያሉ ጥርጣሬዎችን እያደጉ በመምጣታቸው ዘርፉ ላይ ጥላ ማጥላቱንም አንስቷል፡፡

በመሆኑም በጥልቀት ማስተዋል እና ግልጸኝነት አስፈላጊ መሆኑን የጠቆመው ተርቢየም በስውር የኢንተርኔት ምርት እና አገልግሎቶች ላይ የጋራ የሆነ አቋም ሊኖር ይገባል ብሏል፡፡

https://www.infosecurity-magazine.com/news/researchers-call-shared-dark-web/