አሜሪካ ወሳኝ ተቋማቱዋን በኳንተም ኮምፒውተር ዙሪያ ዛሬ ታወያያለች

 

አዲስ አበባ፤መስከረም 14/2011፡-የአሜሪካ መንግስት ዛሬ ሰኞ 14/2011 የኳንተም ኢንፎርሜሽን ሳይንስ እድገትን ዙሪያ ከባለድርሻ አካትን ጋር በእድገቱ እና ተጽእኖው ዙሪያ ስብሰባ ጠርታለች፡፡

ግዙፍ የቴክኖሎጂ እና በኳንተም ኮምፒውቲንግ ዘርፍ የተሰማሩ እንደ ጉግል አይቢኤም( IBM) ጂፒ ሞርጋን ቼዝ እና በዘረፉ አንቱ ተባሉ የአካዳሚክ ግለሰቦች ተካፋይ እንደሚሆኑበት ተጠቁሟል፡፡

የካንተም ኮምፒውተር ዘርፍ ተግባረዊ ሲሆን አሁን ላይ ስራ ላይ ካለው ኮምፒውተር በሚሊዮን እጥፍ የተሸለ አገልግሎቶችን በፍትነት የሚሰጥ ነው፡፡

ይህ ተስፋ ሰጪ የቴክኖሎጂ ውጤት ወደፊት በህክምና ተቋማት፣በኮሚዩኒኬሽን ፣የፋይናንስ አገልግሎት መስጫዎች፣በትራንስፖርት፣በአርተፍሻል ኢንተለጀንስ፣በአየር ንብረት ትንበያ እና በሌሎች መሰል ግልጋሎቶች ላይ እምርታዎችን ያመጣል ተብሎለታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ቴክኖሎጂው ለሃገር ደህንነት አስጊ የሆኑ እጅግ የተራቀቀ በመሆኑ የአሁኖችን ኮምፒውተሮች ደህንነት እና ኮዶችን በቀላሉ መስበር የሚችል በመሆኑ በጉዳይ ትኩረት በማድረግ የሚመለከታቸውን አካላት ለማወያየት ማቀዱ ነው የተነገረው፡፡

ከቴክኖሎጂ ኩባንዎች በተጨማሪም የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታግን)፣የናሽናል ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ፣የኋት ሃውስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ፣ናሳ እንዲሁም የሆምላንድ ሴኪዩሪቲ እና ሌሎች የፌደራል ተቋማት በስብሰባው ይሳተፋሉ፡፡

 

https://www.reuters.com/article/us-usa-computers/key-companies-to-attend-white-house-quantum-computing-meeting-idUSKCN1M4008