በሲንጋፖር የተከሰተው ተደጋጋሚ የሳይበር ጥቃት

በሲንጋፖር በተደጋጋሚ የተከሰተው የሳይበር ጥቃት አገሪቱን ለማውደም የተደራጁ ቡድኖች ሊሆኑ ይችላሉ ሲል መንግስት አስታወቀ፡፡ በተሰነዘረው የሳይበር ጥቃት የጠቅላይ ሚኒስትሩን አካውንት ጨምሮ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ መረጃዎች መበርበራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ጥቃቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያወሳው ዘገባው ችግሩን ለማስወገድ የተጠናከረ ስራ እያከናወነ መሆኑን መንግስት ለአገሪቱ ምክር ቤት ገልጧል፡፡

ስጋቱን ለመቀነስ ለተወሰነ ጊዜ የኢንተርኔት ትስስር መቋረጡንና ካሳለፍነው ታህሳስ ወር ጀምሮ ደግሞ ችግሩን የሚያጣራ ኮሚቴ መቋቋሙ ተጠቁሟል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-singapore-cyberattack/singapore-cyber-attack-has-hallmarks-of-state-linked-group-government-says-idUSKBN1KR0YR