ፌስቡክ አደገኛ ያላቸውን ገጾች እየዘጋ ነው

የፌስቡክ ኩባንያ በማሕበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያስከተሉ ነው ያላቸውን የሀሰት ገጾች (Fake Accounts) መዝጋቱን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም ዙሪያ የምርጫ ስርዓትንና የማሕበራዊ ግንኙነትን አናግተዋል ያላቸውን 32 የሚደርሱ የሀሰት አካውንቶችን መዝጋቱንና በሌሎች ላይ ደግሞ የክትትል ስራ እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡ ኩባንያው  ችግሩን ለማስቀረት ከመቸውም ጊዜ በላይ ርብርብ እያደረገ ሲሆን ሰሞኑን ካምፓኒው 120 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራ ደርሶበት እንደነበር ተተቁሟል፤ ይህም ለቀጣይ የደህንነት ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

ፌስቡክ የ2016ቱን የአሜሪካን ምርጫ ጨምሮ በተለያዩ አገሮች የፖለቲካ ምሕዳር ላይ እጁ አለበት በሚል ሲወቀስ መቆየቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

https://www.nytimes.com/2018/07/31/us/politics/facebook-political-campaign-midterms.html