ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር መስራት አዋጭነት ይኖረዋል፡ የውጭ ኩባንያዎች

ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በጋራ መስራት አገሪቱ ካላት የሕዝብ ቁጥር ጋር ተዳምሮ የተሻለ ገበያ እንደሚኖረው የተለያዩ የውጭ አገር ኩባንያዎች ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ ለረዥም ዓመታት በመንግስት ስር የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዛወር የተሰጠውን ዕድል ተጠቅመው የተለያዩ የውጭ አገር ኩባንያዎች ጥያቄ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ የኢትየጵያን ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ በላቸው መኩሪያን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ጥያቄውን ከሚያቀርቡት መካከል የኬንያው ሳፋሪኮም (Safaricom)፣ የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን (MTN)፣ የፈረንሳዩ ኦሬንጅ (Orange) እና የመሳሰሉት መሆናችው ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የተለያዩ የአገሪቱ ኩባንያዎች ለግሉ ዘርፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ሊዘዋወሩ እንደሚችሉ መንግስት መወሰኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-india-ecommerce/india-looking-to-compel-e-commerce-social-media-firms-to-store-data-locally-idUSKBN1KK0IZ