የሳይበር ጥቃት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚገመት ዶላር ኪሳራ ያስከትላል

ሐምሌ 24/2010 ዓ.ም፡ በዓለም ዙሪያ የሳይበር ጥቃት የሚያስከትለው የኢኮኖሚ ኪሳራ እስከ 817 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሏል፡፡ ቲንክ ታንክ (Think-tank) የተባለው የምርምር ተቋም ደረስኩበት ባለው የጥናት ውጤት መሰረት ችግሩ ከጊዜ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱንና ኪሳራውም ከተጠቀሰው ሊልቅ እንደሚችል መላምቱን አስቀምጧል፡፡ ይሁን እንጂ ስጋቱን ለመከላከል የዓለም ማሕበረሰብ የሰጠው ትኩረት ከሚጠበቀው በታች መሆኑን ተቋሙ ሳያነሳ አላለፈም፡፡

የሳይበር ጥቃት ለዓለም ኢኮኖሚ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

https://www.straitstimes.com/singapore/cyber-attacks-cost-global-economy-817b-a-year-think-tank