ፋይልለስ የተባለ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተባለ

ፋይልለስ የተባለው አዲስ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ የተራቀቀው የጥቃት ስልት ወንጀለኞች የኮምፒውተር ሲስተሞችንና ድረ-ገጾችን ለመቆጣጠር የሚያግዛቸው ሲሆን ይህም ገና አዲስ እና ለከፍተኛ ኪሳራ ሊያጋልጥ የሚችል ነው ተብሏል፡፡ ካተስቶርች (CactusTorch) በመባል የሚጠራው ይህ የሳይበር ጥቃት በዋናነት እንደ ዊንዶው (Windows) ያሉ የኮምፒውተር ውስጣዊ ስርዓትን በማናጋት ለጥቃት የሚያጋልጥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡  ችግሩ በቀጥታ በግለሰቦችና በተቋማት ላይ የሚያነጣጥር መሆኑንም ማካፌላብስ (McAfee Labs) የተባለው የሶፍትዌር ኩባንያ በጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

አዲሱ የጥቃት አይነት በፈረንጆቹ 2017 ብቻ በፊት ከነበረበት በ432 በመቶ ማደጉም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

https://www.gadgetsnow.com/tech-news/fileless-attacks-replacing-traditional-file-based-cyber-attacks-surges-to-432-in-2017-mcafee/articleshow/65165118.cms