ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ አበባ ፡ ሃምሌ 19/2010 ዓ/ም፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦች፡

ከዚህ ቀደም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተሰርቶ በቦሌ መንገድ ተተክሎ የነበረው የመንገድ ዳር የሴኩሪቲ ካሜራ በ2006 ዓ.ም መንገዱ በሚገነባበት ወቅት የተነሳ ሲሆን አሁን ፕሮጄክቱ በአዲስ መልክ ተሰርቶ ካሜራዎቹን የመትከል ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ፕሮጄክቱ በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑንና በቅርቡም እየተከናወነ ያለው ካሜራዎቹን የመትከል ተግባር እንጂ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እንደሚናፈሰው ካሜራዎቹን ከቦታው የማንሳት ተግባር እንዳልሆነ እንገልፃለን፡፡