ጎግል የ5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ተላለፈበት

የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን በጎግል ኩባንያ ላይ የ5.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቅጣት ማስተላለፉን አስታወቀ፡፡ ሕብረቱ ይህን ቅጣት እንዲያስተላልፍ የተገደደው ኩባንያው በፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በመፈለጊያ አፕሊኬሽኑ ላይ የሕብረቱን መመሪያ የሚጻረር ድርጊት ሲሰራ መቆየቱ በማረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡ እንደ ኒዮርክ ታይምስ ዘገባ ጎግል በታሪክ ከፍተኛውን ገንዘብ መቀጣቱ ጉዳት ያስከተለበት ሲሆን በ90 ቀናት ውስጥ ከዘርፉ ተወዳዳሪነት ሊያሽቆለቁል ይችላል ተብሏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክተው የሕብረቱ የሕግ አካላት እንዳሉት ቅጣቱ በቀጠናው የራሱን የበላይነት ለመቆናጠጥ ኩባንያው የሰራውን ስሕተት በአፋጣኝ እንዲያስተካክልና አንዳንድ አፕሊኬሽኖቹንም ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ቅጣቱ በተመሳሳይ ሁኔታ በማይክሮሶፍትና መሰል ኩባንያዎች ላይም ከዚህ ቀደም መፈጸሙን ዘገባው አስታውሷል፡፡

https://www.nytimes.com/2018/07/18/technology/google-eu-android-fine.html