የሳይበር ጥቃትና የሀሰት ወሬዎች በምርጫ ሥርዓት ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ ጥናት አመለከተ

የሳይበር ጥቃትና የሀሰት ወሬዎች በምርጫ ሥርዓት ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ ጥናት አመለከተ

የሳይበር ጥቃትና የሀሰት ወሬ በአገራት የምርጫ ስርዓት ላይ የሚያስከትሉት ተጽዕኖ አሁንም ቀጥሏል ተባለ፡፡ ሰሞኑን በአየርላንድ የሚደረገውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አስመልክቶ የወጣ ሪፖርት እንዳመለከተው የማሕበራዊ ሚዲያዎች በዚህ ምርጫ ላይ ጣልቃ ሊገቡ እንደሚችሉ ምልክቶች መታየታቸው ተረጋግጧል፡፡ ችግሩ ከጊዜ ጊዜ እየሰፋ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ሁኔታው በሕግ አግባብ ሊዳኝ እንደሚገባም በምርመራው ላይ የተሳተፉ አካላት መግለጻቸው በዘገባው ተብራርቷል፡፡

ማሕበርዊ መገናኛዎች በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ውዝግቡ እስካሁን መቀጠሉ ይታወሳል፡፡

https://www.independent.ie/irish-news/politics/cyber-attacks-and-fake-news-pose-risk-to-elections-report-warns-37119547.html