ሲም ካርድ ላይ ያነጣጠረው የሳይበር ጥቃት

ባለፉት ጥቂት ወራቶች ወንጀለኞች ሲም ካርድ (SIM Card) ላይ ያነጣጠረ አዲስ የሳይበር ጥቃት መክፈታቸው ተገለጸ፡፡ አጭበርባሪዎቹ በዋናነት ሲም ካርድን የመረጡት የግለሰቦችን የባንክ አካውንት (መረጃ) በቀላሉ ለማግኘት የታለመ ዘዴ መሆኑንም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ወንጀለኞች በግለሰቦች የእጅ ስልክ ላይ የተለያዩ ኮዶችን በመላክ ጥያቄ የሚያቀርቡ ሲሆን ለዚህ ምላሽ መስጠት ደግሞ ለጥቃት እንደሚያጋልጥ ተደርሶበታል ተብሏል፡፡

የሳይበር ጥቃት አድማሱን እያሰፋና እየተውሰበሰበ በመምጣቱ ማህበረሰቡ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ መያዝና ችግሩን መከላከል ችላ ሊባል የማይገባው ጉዳይ ነው ሲል ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡  

https://indianexpress.com/article/cities/mumbai/card-frauds-cheats-adopt-new-method-block-sim-of-victims-5212191/