የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሃላፊነቱን ሙያዊ በሆነ መንገድ እንደሚወጣ ገለጸ

አዲስ አበባ፤ምሌ 5/2010- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ሃላፊነቱን ሙያዊ በሆነ መንገድ ለመተግበር የሚያስችል አዲስ የመዋቅር እና የአደረጃጀት ለውጦችን አከናውኗል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከዋልታ ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም፡-

• ተቋሙ ፕሮፌሽናል ስራዎችን የሚሰራ ተቋም በመሆኑ ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ነጻ ነው፡፡

• ማንኛውም አካል በፖለቲካ ምህዳሩ ስልጣን ይያዝ የተቋሙ ድርሻ ሃገርን እና ህዝብን ማገልገል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

• ሳይንሳዊ የሆነ ፕሮፌሽናል ተቋም ለመገንባትም በአዋጅ የተሰጠውን ሃላፊነት ወደ ተግባር መለወጥ የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡

• የሃገርን ደህንነት ለመጠበቅ ተመሳሳይ ተልዕኮ ካላቸው ተቋማት ጋር በትብብር ይሰራል፡፡ የትብብር ስራውም ሁሉም የራሱን ሃላፊነት በማወቅ የጋራ በሚያደርገን ጉዳይ ላይ በመደመር ይሰራል ብለዋል፡፡

• ከዚህ ቀደም በነበረው የአመራር ስርዓት የታየውን ከተልዕኮ ውጪ የነበሩ ጣልቃ ገብነት ጋር ተያይዞ የተሰሩ ስህተቶችን በማረም ለሃገር እና ለህዝብ የሚበጁ ስራዎች ይሰራሉ ሲሉ አሳውቀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

https://youtu.be/Vm20dAQ_6tM