ለንዶን ዓለም አቀፍ የሳይበር ወንጀል ዳኝነት መስጫ ፍርድ ቤት ልትገነባ ነው

ሐምሌ 2010- በአሁኑ ሰዓት የሳይበር ደህንነት ወንጀል እጅግ እየሰፋ እና በአመት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦች በተለያዩ መንገዶች እየተጭበረበረ ይገኛል፡፡ 
ይህን ተከትሎም በእንግሊዝ ያሉ ደህንነት ባለሙያዎች አለም አቀፍ የሳይበር ወንጀል ላይ ፍርድ መስጠት የሚያስችል የህንጻ ግንባታ ፍቃድ የሃገሪቱ መንግስት መፍቀዱን አመስግነዋል፡፡ 
ይህ በለንደን የሚገነባው ህንጻም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚ የሆነ የሳይበር ወንጀል ፍርድ መስጫ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡

እ.ኤ.አ በ2025 ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይችላል የተባለው ህንጻም እየተፈጸሙ ያሉትን የሳይበር ማጭበርበር እና የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመከላከል ለንደንን ቀዳሚ ከተማ እንደሚያደርጋት ታምኖበታል፡፡