ባንኮች የሳይበር ጥቃት ቢያጋጥማቸው ለማገገም የሚያስችላቸው ዕቅድ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጸ

በታላቋ ብሪታንያ የሚገኙ ባንኮች በሚጠቀሙት አሰራር ላይ የሳይበር ችግር ቢያጋጥማቸው በፍጥነት ወደ ነበሩበት ለመመለስ ያላቸውን ዕቅድ ማሳወቅ አለባቸው ተባለ፡፡ የብሪታንያ ፋይናንስ ባለስልጣን (FCA) ከለንደን ባንክ ጋር በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳሳሰቡት በአገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፣ የገንዘብ ተቋማትና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በቴክኖሎጅ አሰራራቸው ዙሪያ የሳይበር ጥቃት ቢገጥማቸው የራሳቸው የማገገሚያ ዕቅድ እንዲኖራቸው አሳስበዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ተቋማቱ ይህን በተመለከተ ያላቸውን ዕቅድም በሶስት ወር ውስጥ እንዲያሳውቁ የጊዜ ገደብ ተቀምጦላቸዋል ተብሏል፡፡

የገንዘብ ድርጅቶቹ ከችግሩ መልሶ ለማገገም (resilience) ራሳቸውን እንዲያበቁና ኃላፊነት በመውሰድ አገርን ከኪሳራ መታደግ እንዳለባቸውም ተጠቅሷል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-britain-boe-banks/uk-banks-told-to-show-their-backup-plans-for-tech-shutdowns-idUSKBN1JV0X2