የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ሆን ብለው ሰዎችን ለሱስ ተጠቂ እንደሚያደረጉ ተገለጸ

ሰኔ 27/2010፡ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የፋይናንስ ገቢያቸውን ከፍ ለማድረግ በማሰብ በሚያቀርቧቸው የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎችን ተጠቃሚዎች በሱስ እንዲያዙ የሚያደረጉ አመራጮችን እንደሚጠቀሙ የቀድሞ የሲልከን ቫሊ አባል የነበሩ የዘርፉ ጠበብቶች ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱም ባህሪያዊ ኮኬይን የሆኑ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ እና ተጠቃሚዎች በየደቂቃው የማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዲጎበኙ እና የሱስ ተጠቂ እንዲሆኑ ማድረጉን የቀድሞ የሞዚላ እና ጃውቦን ባልደረባ የነበሩት አዛ ራስኪን ይናገራሉ፡፡

በእያንዳንዱ የሞባይል ስክሪን ጀርባ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢንጂነሮች ተጠቃሚዎችን ሱስ የማስያዝ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ መተግበሪያ የማበልጸግ ስራዎችን በመከወን ላይ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 የቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ መሪ ሆነው በሰሩበት ስራ ተጠቃሚዎች ያለገደብ ፍለጋዎችን እና አሰሳዎችን እንዲያደረጉ የሚገፋፋ አማራጭ ተግባራዊ ማድረጋቸውን የተናገሩት ሚስተር ራስኪን አሁን ላይ በአፕሊኬሽኖች ላይ እየተተገበሩ ያሉ አማራጮችም አብዛኛዎቹ ሱስ የሚፈጥሩ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

እነዚህ አማራጮችም ተጠቃሚዎች ያለማቋረጥ ፍለጋቸውን እንዲቀጥሉ የሚገፋፋ ሲሆን በተወሰነ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድረገው እንዳይጠቀሙ ያደርጋል ብለዋል፡፡ በዚህም ሰዎች አእምሮአቸውን ተቆጣጥረው ፍለጋቸውን ማቆም ካልቻሉ ያለ እረፍት መረጃዎችን በመፈለግ ይባዝናሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚያቀርቧቸው የመማረኪያ አማራጮች መካከልም የወድጀዋለሁ (Like's) አማራጭ አንዱ ሲሆን በሌላ መልኩ አሪፍ ነው (thumbs-up sign) ኸርት (hearts) አልያም ሪቲዩት (retweets) በሚል እንደሚቀርቡ ተጠቅሷል፡፡

 

በቅርቡ እየወጡ ያሉ አንዳንድ ጥናቶችም እንደሚያሳዩት ከሆነ የማህበራዊ ሚዲያዎችን በከፍተኛ መጠን መጠቀም  ከድብርት፣ የብቸኝነት ስሜት እንዲሁም ሌሎች መሰል የአእምሮ ችግሮች ጋር ተያዥነት እንዳለው እየጠቆሙ ይገኛሉ፡፡  

https://www.bbc.com/news/technology-44640959