የግል የኢ-ሜይል መልዕክቶች በሶስተኛ ወገን እንደሚነበቡ ጉግል ገለጸ

ሰኔ 27/2010፡ ግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም ጉግል በጂ-ሜይል አማካኝነት የመንላላካቸው የኢ-ሜይል መልዕክቶች በሶስተኛ ወገን የመተግበሪያ አበልጻጊዎች የመነበብ እድል እንዳላቸው አሳውቋል፡፡

አካውንታቸውን በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ጋር ያገናኙ አካላት ሳይታወቅ ለሰዎቹ በጂ-ሚይል የተላላኩትን የኢ-ሜይል መልእክቶች እንዲያነቡ ፍቃድ እንደሚሰጡ አሳውቋል፡፡

ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነት ለመመስረት በምናስብበት ወቅት አካውንታችንን እንድናካትት ይጠይቃሉ፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከልም ሶስተኛ ወገኖችን የኢ-ሜይል መልዕክቶችን ከማንበብ በተጨማሪ መልዕክት መላክን፣ መሰረዝን እና መልእክት የማስተዳደር ተግባርን እንደሚከውኑ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተጠቃሚዎች የኢ-ሜይል አድራሻዎች ለሶስተኛ ወገን አገልግሎት ለማግኘት በሚል አሳልፈው ሲሰጡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደረጉ ይገባል፡፡

ጂ-ሜይል ታዋቂ የኢ-ሜይል መላላኪያ አማራጭ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

https://www.bbc.com/news/technology-44699263