የኢመደኤ አመራርና ሠራተኞች ደም ለግሰዋል

ሰኔ 20/2010 ዓ/ም፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) አመራርና ሠራተኞች ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ "ለውጥን እንደግፍ፣ ዲሞክራሲን እናበርታ" በሚል መሪ ቃል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ እና መንግስታቸው እየወሰደ ላለው የለውጥ እርምጃ ድጋፍና ምስጋና ለመስጠት በተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ደም ለግሰዋል፡፡ በተመሳሳይም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመገኘትም ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በመጎብኘት አበረታተዋል፡፡

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዕለቱ ደም ከለገሱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢመደኤ እንደ ተቋም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እየወሰዷቸው የሚገኙትን የለውጥ እርምጃዎች እንደሚደግፍና፤ ከዚህ በተጻራሪ የቆሙ ሃይሎችንም በጽኑ እንደሚቃወም ገልጸዋል፡፡ የሕብረተሰቡ አካል የሆነው ኢመደኤም በወቅቱ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ ይህን የደም ልገሳ ፕሮግራም እንዳዘጋጀ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡https://youtu.be/QAAsF7rZ_4k