ኢመደኤ ራዕይና ተልዕኮውን በአዲስ መልኩ ከልሷል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) እያካሄዳቸው ካሉ የለውጥ እርምጃዎች መካከል፤ ኤጀንሲው በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነቶች ላይ ብቻ በማተኮር እንዲሰራ ማድረግ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በዚህም መሰረት የኤጀንሲውን ራዕይና ተልዕኮም በዚሁ አግባብ መቃኘት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ኤጀንሲው ራዕይና ተልዕኮውን በአዲስ መልክ ከልሶ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ በዚህም መሰረት የኤጀንሲው፡-https://youtu.be/a8XzsqU9pZs

 

  • ራዕይ

በ2017 ዓ/ም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለው እና በሀገሪቱ ህዳሴ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ብሄራዊ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ተቋም እውን ማድረግ፡፡  

  • ተልዕኮ

የአገሪቱን ኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማትን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ፡፡

 

  • ስትራቴጂክ እሴቶች
  • ተአማኒነት
  • ሁሌም መማርና ማደግ
  • ልዩነት መፍጠር
  • ተጠያቂነት