በፕሮጀክቶች የሥራ እንቅስቃሴዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዲሁም ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ሌ/ኮሎኔል አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ፤ የተለያዩ የኤጀንሲውን ፕሮጀክቶችንና  የስራ እንቅስቃሴን ቅደም ተከተል በመስጠት በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡  አመራሮቹ በተለያዩ ሳይቶች ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በዚህም ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ደረጃ፣ በተጨባጭ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን፣ ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን አካሄድና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ በፕሮጀክቶቹ  አስተባባሪዎች በኩል ገለጻ ተደርጓል፡፡