ዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው

የ2018 ዓለም አቀፍ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጉባኤ በዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ሕብረት (ITU) አስተናጋጅነት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ጉባኤው ከዛሬ ግንቦት 7 እስከ ግንቦት 9/2010 ዓ.ም ድረስ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የጉባኤው ዋና ዓላማ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እድገት ለዓለም ደህንነትና የዘላቂ ዕድገት ፕሮግራምን ለማሳካት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለመ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ጤና፣ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ሳተላይት ምስል/ፎቶ፣ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ዘመናዊ ከተሞችና ማህበረሰብ፣ እንዲሁም አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ተዓማኒነቱ በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

ለሶስት ቀን የሚቆየው ጉባኤው የታለመለትን ግብ ይመታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ከመላው ዓለም በፍላጎታቸው የሚሰባሰቡ አካላት ናቸው ተብሏል፡፡

https://www.giplatform.org/events/ai-good-global-summit-2018