አዲሱ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር በአዲሱ የሕግ ማዕቀፍ ላይ ልዩነት እንደሌላቸው ገለጹ

በማሌዥያ የሀሰት ወሬዎችን አስመልክቶ ለአጭር ጊዜ ስራ ላይ በነበረው አዲሱ የሕግ ማዕቀፍ ላይ ልዩነት እንደሌላቸው አዲስ የተሾሙት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር  አስታወቁ፡፡ አሶሼትድ ፐረስን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ሲ.ኔቲ (cnet) በድረ-ገጹ እንዳሰፈረው በማሌዥያ ከአንድ ወር በፊት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መምበር የመጡት ማሀዚር ማሀመድ በማሕበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የሀሰት ዜናዎችን በተመለከተ የወጣው ሕግ ባለበት እንዲቀጥል አረጋግጠዋል ብሏል፡፡ በዚህ ዙሪያ ገለጻ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕጉ ተቀባይነት ያለው መሆኑን በማመን መንግስትና የሚዲያ አውታሮች የሀሰት ወሬዎችን በመለየት ችግር ፈጣሪ ወንጀለኞችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ  አሳስበዋል፡፡

ማሌዥያ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2018 በማሕበራዊ መገናኛዎች የሚሰራጩ የሀሰት ወሬዎችን አስመልክቶ ያወጣቸው የሕግ ማዕቀፍ እስከ 6 ዓመት ለስር ሊዳርግ እንደሚችል በዘገባው ተጠቅሷል፡፡   

https://www.cnet.com/news/malaysias-fake-news-law-is-here-to-stay-new-prime-minister-says/