የአውሮፓ ሕብረት አዲስ ግላዊ የመረጃ አጠባበቅ የሕግ ማዕቀፍ አጸደቀ

የአውሮፓ ሕብረት አዲስ ግላዊ የመረጃ አጠባበቅ የሕግ ማዕቀፍ EU General Data Protection Regulation (GDPR) ማጽደቁን አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት በማሕበራዊ መገናኛዎች የሚሰራጩ መረጃዎች ለአገራት ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ ሕብረቱ ችግሩን ለመከላከል የሚያስችል ሕግ ለማውጣትና ተግባራዊ ለማድረግ መገደዱን አብራርቷል፡፡ ማዕቀፉን ለማዘጋጀት ለአራት ዓመት ያክል ልዩ ልዩ ስራዎች መከናወናቸውን የሚጠቅሰው ዘገባው ሕጉ በፈረንጆቹ ሚዝያ 14 ቀን 2010 ዓ.ም ለሕብረቱ ፓርላማ ቀርቦ ጸድቋል ተብሏል፡፡ የተቋቋመው የሕግ ማዓቀፍ (GDPR) ከዚህ በፊት የነበረውን ዳታ ፕሮቴክሽን ዳይሬክቲቭ (DPD) ተክቶና ተሻሽሎ የቀረበ ሲሆን በተለይም በማሕበራዊ መገናኛዎች የሚደርሰውን የመረጃ ብርበራ ለመከላከል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አዲሱ የሕግ ማዕቀፍ በፈረንጆቹ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተጠቅሷል፡፡

https://www.eugdpr.org/