ካምብሪጅ አናሊቲካ መዘጋቱ ተገለጸ

የፌስቡክ ደንበኞችን አካውንት ያለራሳቸው ፈቃድ ለፖለቲካ መቀስቀሻነት ያዋለው ካምብሪጅ አናሊቲካ የተባለው የፖለቲካ አማካሪ ኩባንያ መዘጋቱ ተገለጸ፡፡ ኩባንያውን ለዚህ ያበቃው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፌስቡክ ደንበኞችን የግል አካውንት ያለፈቃዳቸው ብርበራ አድርጓል በሚል በደረሰበት ክስ ነው ተብሏል፡፡ ሁኔታውን አስመልቶ አስተያየት እንዲሰጥ የተጠየቀው ኩባንያው በግልጽ የታወቀ ጥፋት መኖሩን ባያምንም የመገናኛ ብዙሃን ባደረሱት የነቀፋ ዘመቻ ደንበኞቹ መሸሻቸው ለድርጅቱ መዘጋት እንደምክንያት ማቅረቡን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ካምብሪጅ አናሊቲካ በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ላይ ጣልቃ ገብቷል በሚል በደረሰበት ጫና ለኪሳራ መዳረጉን ያወሳው ዘገባው በኬንያ፣ በናይጄሪያ እንዲሁም ታላቋ ብሪታንያ ከአውሮፓ ሕብረት ለመውጣት ያደረገችውን የሕዝበ ውሳኔም ኩባንያው በአማካሪነት መስራቱንም በዘገባው ተነስቷል፡፡ 

መቀመጫውን በታላቋ ብሪታንያ ያደገው ካምብሪጅ አናሊቲካ ትናንት ምሽቱን ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን ዘጋርዲያን በድረ-ገጹ አስፍሯል፡፡

http://www.bbc.com/news/business-43983958