ዋና ዳይሬክተሩ ከመካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ ጋር የትውውቅ መድረክ አካሂደዋል

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዓርብ ሚያዚያ 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከኤጀንሲው መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ጋር የትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡ በእለቱ የቀድሞዎቹ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች፤ ኮሎኔል ታዜር ገ/እግዚአብሔር፣ አቶ ቢንያም ተወልደ እና አቶ ሲሳይ ቶላ በይፋ ተሸኝተዋል፡፡ በተመሳሳይ አዲስ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው  የተሾሙት ሌ/ኮሎኔል አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ከመካከለኛና ከፍተኛ አመራሩ ጋር ትውውቅ በማድረግ ስራቸውን ጀምረዋል፡፡

በዕለቱ ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላፉት መልዕክት፤ ኤጀንሲው የያዘው ብሔራዊ የሳይበር ኃይል ግንባታ ራዕይ ከግብ እንዲደርስ አዲሱ አመራር ከተቋሙ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በላቀ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡