ዓለም አቀፍ ዲጂታል ቤተ-መጽሃፍ ለመክፈት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አገር ሆና ተመርጣለች

ዓለም አቀፍ ትብብር ለመፃህፍት የተሰኘው ጥምረት አዲሱን ዓለም አቀፍ ዲጂታል ቤተ-መጽሃፍ ለመክፈት ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አገር ሆና መመረጧን ገለጸ፡፡ ቤተ-መጽሃፍቱ በሰባት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የተለያዩ መፃህፍት እንዲሁም ለእረፍት ጊዜ ንባብ የሚሆኑና በ3 የአፍሪካ ቋንቋዎች የተፃፉ የታሪክ መፃህፍት ይኖሩታል፡፡

በአሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ እንግሊዝና ሌሎች አገራት ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፉ ጥምረት በኢትዮጵያ የሚከፍተው ይኸው ቤተ-መጽሃፍ ህፃናትና ወጣቶች ደረጃቸውን የጠበቁ መፃህፍት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

አዲሱ ዲጂታል ቤተ መፃህፍት የዓለማችን ህፃናትና ወጣቶች ለንባብ የሚያስፈልጓቸውን መፃህፍት ለማቅረብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ ትብብር ለመፃህፍት የተሰኘው ጥምረት ደረጃቸውን የጠበቁ የመማርያ መፃህፍትን በማሰባሰብ በዌብሳይትና ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በዲጂታል እንዲሁም በጥራዝ መልኩ እንዲሰራጩ ይሰራል፡፡

በሂደት መፃህፍትን ከየአካባቢው ባህል ጋር በማዛመድ ከ300 በላይ በሚሆኑ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች የማስተርጎም እቅድ እንዳለም ተገልጿል፡፡

ሰባቱ ቋንቋዎች አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሱማሊኛ፣ ሲዳምኛ፣ ወላይትኛ እና ሀዲይኛ መሆናቸው ታውቋል፡፡

http://www.itnewsafrica.com/2018/04/ethiopia-selected-as-the-first-country-to-launch-global-digital-library/