አገሪቱ አዲስ የሳይበር ማዕከል ልትገነባ ነው

በታላቋ ብሪታንያ በ13.5 ሚሊዮን ፓውንድ አዲስ የሳይበር ደህንነት ማዕክል ሊገነባ መሆኑን የአገሪቱ መንግስት አስታቀ፡፡ መንግስት ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘረውን የሳይበር ጥቃት በሙሉ ብቃት ለመመከት የመዕከሉ አስፈላጊነት ወሳኝ መሆኑን ቀድሞ በመገንዘቡ ነው ሲል  ዘቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡ በሎንደን ከተማ የሚገነባው አዲሱ የሳይበር ማዕከል በዋንነት በአገሪቱ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋማት ላይ በሳይበር ጥቃት ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ  ለመከላከል ታስቦ እንደሆነም ታውቋል፡፡ የብሪታንያ መንግስት አዲስ በሚገነባው የሳይበር ማዕከል ከፍተኛ ተስፋ እንደሚጥልበትና ከአገሪቱ አልፎ ዓለማቀፍ የሳይበር ደህንነት ኢንዱስትሪውን በአንድ እርምጃ ከፍ ያደረገዋል ሲል አስታውቋል፡፡ አያይዞም የሚገነባው ማዕከል በፈረንጆቹ 2018 ለሳይበር ደህንነት ስራ ዓለም 69 ቢሊዮን ዩሮ ያስፈልጋታል ተብሎ ከተተነበየው መካከል የሚመደብ  መሆኑንም ዘገባው ሳያነሳ  አላለፈም፡፡ 

የብሪታንያ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ሴንተር በአገሪቱ የቢዝነስ ተቋማት ላይ ልዩ ልዩ የሳይበር ጥቃቶቾ ሊሰነዘሩ እንደሚችሉ በግኝቱ ማረጋገጡን መረጃው አስታውሷል፡፡ 

https://www.telegraph.co.uk/technology/2018/04/10/government-launches-135m-cyber-security-centre-olympic-park/