የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ለኤሌክትሮኒክ ንግድና አገልግሎቶች መሳለጥ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል

በሀገራችን የኤሌክትሮኒክ ንግድን እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዙ የመንግስት አገልግሎቶችን ለማበረታታት ምቹ የሕግ ማዕቀፍ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤ በኤሌክሮኒክ መልዕክት ልውውጥ ወቅት የተሳታፊዎችን ማንነት፣ የመልዕክቶችን ትክክለኛነት እና አለመካካድን በማረጋገጥ መተማመን ለመፍጠር የሚያስችሉ የኤሌክትሮኒክ ፊርማዎችን ሕጋዊ እውቅና መስጠት በማስፈለጉ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/210 ባሳለፍነው የካቲት 2010 ዓ.ም መታወጁ ይታወሳል፡፡ አዋጁ ለኤሌክትሮኒክ ፊርማ ሕጋዊ ዕውቅናን የሚሰጥ ሲሆን ይህም በሀገሪቱ ለሚከናወኑ የኤሌክትሮኒክ ንግድና አገልግሎቶች መሳለጥ ወሳኝ ሚናን የሚጫወት ነው፡፡

የአዋጁን ሙሉ ቅጂ ለማግኘት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡