በፌስቡክ ላይ እምነት እያጡ መምጣታቸውን ደንበኞች ተናገሩ

ሰሞኑን በአሜሪካና በጀርመን በተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት አብዛኞቹ የአገራቱ ዜጎች በፌስቡክ ላይ እምነት ማጣታቸውን ተናገሩ፡፡

የሕዝብ አስተያየትን መሰረት አድርጎ በየሳምንቱ የሚታተም አንድ መጽሔትን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ እንደዘገበው ከግማሽ የማያንሱ የአሜሪካን ኑዋሪዎች ፌስቡክ በዜጎች የግል ነጻነት ላይ እያደረሰ ያለው ተጽዕኖ እንዳሰጋቸውና እምነት እንዳጡበት መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ 60 ከመቶ የሚሆኑት የጀርመን ዜጎች በበኩላቸው ግዙፉ የማሕራዊ ሚዲያ ፌስቡክ እያስከተለ የሚገኘው አሉታዊ ተጽኖ እንዳሳሰባቸውና በተለይም በዲሞራሲ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ጠላሸት እንዳያጠላ ስጋታቸውን መግለጻቸውን ዘገባው አስነብቧል፡፡ ስጋቱ በዚህም ሳያበቃ አንዳንድ የአሜሪካ የምክር ቤት አባላትም በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰነዘሩ ሲሆን  የፌስቡክ ኩባንያ ለሕግ እንዲቀርብና እንዲያውም ሁኔታው ተመርምሮ እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ መወሰድ አለበት እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ስጋቱን አስመልክተው የፌስቡክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ለተለያዩ ሚዲያዎች  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ችግሩን እንደሚያስተካክሉ ቃል ቢገቡም ዜጎች በኩባንያው ላይ እምነት እንደሌላቸው እየተነገረ ነው፡፡

ሰሞኑን ካምብሪጅ አናሊቲካ በተባለ የፖለቲካ አማካሪ ድርጅት በኩል የግለሰቦች የፌስቡክ የግል አካውንት ያለነሱ ፈቃድ ለምርጫ ቅስቀሳ ውሏል በሚል ኩባንያው ላይ ከፍተኛ ወቀሳ መቀስቀሱን  ይታወሳል፡፡ 

https://www.reuters.com/article/us-facebook-cambridge-analytica-apology/americans-less-likely-to-trust-facebook-than-rivals-on-personal-data-idUSKBN1H10AF