የፌስቡክ ኩባንያ ባለአክሲዎኖች ከባለቤትነታቸው እየለቀቁ ነው

ከፌስቡክ ኩባንያ ጋር ይሰሩ የነበሩ አጋር ኩባንያዎች ከአክሲዮን ባለቤትነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው እየለቀቁ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ከኩባንያው ጋር በሽርክና ሲሰሩ የቆዩት አክሲዮኖች ለመልቀቅ የወሰኑት በሀገረ እንግሊዝ  የሚገኘው ካምብሪጅ አናሊቲካ የተባለ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም 50 ሚሊዮን የሚሆኑ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የፌስቡክ አድራሻ ያለደንበኞች ፈቃድ ለ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ቅስቀሳ ተጥቅሞበታል የሚል ምርመራ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡ እንደ ቢ.ቢ.ሲ ዘገባ 6.7 ከመቶ የአክሲዮን ባለቤቶች በሁለት ቀናት ውስጥ ሲወጡ፤ የኩባንያው ገቢም በ50 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አሽቆልቁሏል ተብሏል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የፌስቡክ ኩባንያ ችግር ውስጥ መሆኑን ያወሳው ዘገባው የተከሰተውን ሁኔታ ለመወያየት ስብሰባ ቢጠራም የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ውይይቱን በቅጡ ለመምራት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ፌስቡክ የችግሩ ተጠያቂ የሆነው ዋናው ምክንያ ድርጅቶች በአገራት ምርጫ ላይ በፌስቡክ የተለያዩ ችግሮችን ሲፈጥሩ ሁኔታውን ቀድሞ ቢያውቅም አስፈላጊ እርምጃዎችን ባለመውሰዱ ነው፡፡

ፌስቡክ በዓለም አገራት በተደረጉ 200 ምርጫዎች ላይ እክል ፈጥሯል ያለው ዘገባው በአውሮፓ፣ በኢሲያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍሪካ አገራት ምርጫዎች ላይም ተመሳሳይ ችግር ሳይፈጥር እንዳልቀረ ተነስቷል፡፡

www.bbc.com