በላቲን አሜሪካ የሳይበር ደህንነት ችግር ለዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ

በላቲን አሜሪካ ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት በዲጅታል ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ሲል የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም በድረ-ገጹ አስነብቧል፡፡ በአሕጉሪቱ ከመንግስት እስከ ግል ድርጅቶች ድረስ ዲጅታልን ጥቅም ላይ በማዋል ኢኮኖሚን ለማበልጸግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ለሳይበር ደህንነት የተሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ የታለመውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ አዳጋች ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ኢኮኖሚን ለማሳደግ ዲጅታላይዜሽን የማይተካ ሚና ቢኖረውም የሳይበር ደህንነት ችግር ግን አሳሳቢ ነው ያለው መረጃው በአሁኑ ወቅት በየቀኑ እስከ 20 ቢሊዮን የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች በዓለም ላይ እንደሚሰነዘሩ በጥናት ተረጋግጧል ተብሏል፡፡ በላቲን አሜሪካ ከፓናማ አስክ ሪዮ ዴጄኔሪዮ ከተሞች ስማርት ቴክኖሎጅዎች በስፋት ስራ ላይ እየዋሉ ሲሆን ለትራፊክ ደህንነት፣ ለአየር ንብረት ጠቋሚ መሳሪያነትና የመሳሰሉት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሆኖም የቴክኖሎጅ መሳሪያዎች በብዛት ጥቅም ላይ በዋሉ ቁጥር ለሳይበር ደሕንነት ችግር መጋለጣቸው ከፍተኛ መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት ተጠቁሟል፡፡ ለሳይበር ደህንነት ተገቢውን ትኩረት ካለተሰጠ በስተቀር የኢኮኖሚው ማደግ ቀርቶ ለሌላ ኪሳራ ሊያስክትል እንደሚችልም ዘገባው ሳያነሳ አላለፈም፡፡ ለዚህ ማሳያው ደግሞ በ2017 በተደረጉ የሳይበር ጥቃቶች 53 በመቶ የሚሆኑት በፋይናንሱ ዘርፍ መሰንዘራቸው በኢኮኖሚው ዘርፍ የተጋረጠ ችግር ነው ሲል መረጃው ያነሳል፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ የላቲን አሜሪካ አህጉር በቴክኖሎጅው ዘርፍ ጥሩ እየተራመደ ቢሆንም በሳይበር ደህንነቱ ብዙ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች  አሁንም ይታይበታል ተብሏል፡፡

ላቲን አሜሪካ በዓለም ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት የሚያስተናግድ አህጉር ሲሆን የዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ የቴክኖሎጅውን አቅም ያገናዘብ የሳይበር መከላከያ አለመኖሩ እንደምክንያት ተነስቷል፡፡  

https://www.weforum.org/agenda/2018/03/this-is-the-biggest-threat-to-latin-america-s-digital-transformation