አፕል ሁሉም የማክ ምርቶቹ የችፕ ክፍተት ሰለባ መሆናቸውን ገለጸ

 

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ተቋም አፕል የአይፎን (iPhones)፣ አይፓድ (iPads) እና ማክ (Mac) ኮምፒውተሮቹ በሜልትዳውን እና ስፔክተር የችፕ ክፍተቶች ሰለባ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኮምፒውተር ማዕከላዊ ፕሮሰሲንግ ዩኒት (CPU) ላይ የተገኙትን የደህንነት ክፍተቶ ለመሙላት ተቋማት በከፍተኛ ሩጫ ላይ ናቸው፡፡

የክፍተቱ (bugs) ሰለባ የሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ እና የኢንቴል (Intel) እና ኤ.አር.ኤም (ARM) ቺፕ ተጠቃሚ የሆኑ ዘመናዊ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች መጠቀሚያ ቴክኖሎጂዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡

አፕልም ለተጠቃሚዎቹ የክፍተት (flaws) መሙያ የለቀቀ ሲሆን ተጠቃሚዎቹ ከታማኝ ምንጮች ብቻ በማውረድ መጠቀም ይገባቸዋል ብሏል፡፡ ተቋሙ መከላከያ ካቀረበላቸው መካከልም ለአይፎን እና አይፓድ ስርዓተ ክወና (operating systems)፣ ለiOS 11.2፣ የMacOS 10.12.2 ለሆኑት ለማክቡክ (MacBooks) እና ለአይማክ (iMacs) ምርቶች ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑና የኢንቴል (Intel) እና ኤ.አር.ኤም (ARM) ቺፖችን ለምርቶቻቸው የሚጠቀሙ ኩባንያዎች የጥቃት ተጋላጭነቱን ለመከላከል በከፍተኛ ደረጃ በስራ ተጠምደዋል፡፡

http://www.bbc.com/news/technology-42575033