ጀርመን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ የጥላቻ ወሬዎችን አስመልክቶ ያወጣችውን ሕግ ተግባራዊ ልታደርግ ነው

 

ጀርመን በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ የጥላቻ፣ የዘረኝነትና መሰል ይዘት ያላቸውን ወሬዎች አስመልክቶ ያረቀቀችውን ህግ በፍጥነት ተግባራዊ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ ባሳለፍነው ሰኔ 2017 የወጣው ይህ ህግ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2017 ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ዕቅድ ተይዞ እንደነበር የቢ.ቢ.ሲ ዘገባ አስታውሷል፡፡ በሕጉ መሰረት የይዘት ችግር አለባቸው የተባሉ መልዕክቶች በ24 ሠዓት ውስጥ የማይነሱ ከሆነ ኩባንያዎችን (ይዘቱ የተለጠፈባቸውን ኩባንያዎቸው) እስከ 44.3 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚቀጡ ያትታል፡፡ በመሆኑም ሕጉ በተያዘለት የጊዜ ቀመር መሰረት ስራ ላይ ባይውልም አሁን ግን በፍጥነት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ስምምነት ላይ መደረሱን የአገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በተለይም ከ2 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላቸው ሳይቶች በዚህ ሕግ ተካተዋል ያለው ዘገባው በዋናነትም እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ዩቱብ እና የመሳሰሉትን ተጠያቂ ያደርጋል ተብሏል፡፡ ሆኖም የሕጉ ተግባራዊ መሆን የሰዎችን የመናገር ነጻነት እንዳይጋፋ ግን ስጋት ላይ የጣላቸው አካላት መኖራቸውን የቢ.ቢ.ሲ ዘገባ ሳያነሳ አላለፈም፡፡

የአውሮፓ ሕረት ኮሚሽን የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጥላቻ ያነገቡ መልዕክቶችን ፈጥነው እንዲያወርዱ የሚያዝ መመሪያ (Guideline) ከዚህ ቀደም ማስቀጡንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

http://www.bbc.com/news/technology-42510868