ተቋርጦ የነበረው የአንጎላ ሳተላይት ግንኙነት መመለሱ ተነገረ

 

በሩሲያው የህዋ ምርምር ተቋም ሮስኮስሞስ (Roscosmos) አማካኝነት ወደ ህዋ ተልካ የነበረችው የመጀመሪያዋ የአንጎላ ሳተላይት ግንኙነት ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ወደ ህዋ ተልካ የነበረችው የመጀመሪያዋ የአንጎላ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት አንጎሳት-አንድ (Angosat-1)  በምድር ምህዋር ላይ ከደረሰች በኋላ ግንኙነቱ ለሁለት ቀናት ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ለሁለት ቀናት ከሳተላይቷ ጋር ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት መመለሳቸውን የሩሲያ ሳይንቲስቶች አሳውቀዋል፡፡

አንጎሳት-አንድ (Angosat-1) በአንጎላ ያለውን የሞባይል እና የኢንተርኔት ተግባቦቶችን ከማሳደጉ በተጨማሪ በሬዲዮ እና በቴሌቭዥን ዘርፍ ያለውን እድገት ለማጎልበት ወደ ህዋ የተላከች ናት፡፡ እስካሁን የሳተላይቱ ግንኙነት በወሳኝ ሰዓት የተቋረጠበት ምክንያት መረጃ አለመሰጠቱን እና የችግሩን ምክንያት ሩሲያ ማጣራት መጀመሯ ተነግሯል፡፡

http://www.bbc.com/news/technology-42510865